=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
![]() ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ! ![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። |
---|
በቁርአን ሱረቱል ኢንሳን ቁጥር 17 ላይ ዝንጅብል አንዱ የጀነት መጠጥ እንደሆነ ተገልፃል። ዝንጅብል ለጤና ግልጋሎት ለ 5000 ዓመት ያህል ሲያገለግል የኖረ ሲሆን ተመራጭ የህክምና እፅም ነው።
የተፈጨ ደረቅ ዝንጅብልን ለጤና መጠቀም ጠቃሚ ሲሆን ትኩስ ዝንጅብልን መጠቀም ተመራጭ ያደርገዋል።
ዝንጅብልን በጥብጦ መጠጣት የምራቅ አመንጭ እጢዎችን ያነቃቃል ፤ ሳልን ያለዝባል ፤ የጉሮሮ መከርከርን ወይም የጉሮሮ መጉረብረብን ያሽላል።
ዝንጅብል በጉዞ ወቅትና በኬሚካዊ ህክምና ወይም በሌሎች አጋጣሚወች የሚፈጠርን የማጥወልወል ስሜትን ለማከም እንደሚረዳ በዘርፈ ብዙ ጥናቶች ለማረጋገጋገጥ ተችሏል።
ከዚህም ባሻገር የተለያዩ የአለርጅክ አይነቶችን ፣ የጡንቻ መሸማቀቅን እና የሆድ ቁርጠት ላለባቸው ሰዎች እንደ መድሐኒትነት ያገለግላል።
ዝንጅብል ልዩ ኢንዛይም የያዘ ሲሆን በምግባችን ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖችን እንዲብላሉ የሚያድርግና የተመገብናቸው ምግቦች ቶሎ ብለው እንዲፈጩ ይረዳል። ለዚህም ነበር የጥንት ግሪካውያን ከበድ ያለ ምግብ ከተመገቡ ብኋላ ዝንጅብል ይበሉ ወይም ይጠጡ የነበረው።
ዝንጅብል የኮሌስትሮልና የደም መርጋትን እንደሚያስቀር ተረጋግጧል። ዝንጅብል ውጥረትን ፣ የራስምታትን ፣ የጥርስ በሽታን ለማሻልና ጥሩ የሆነ እስትንፋስ እንዲኖረን የሚረዳ ሲሆን የካንሰር እጢዎችን እድገት ይገድባል።
ዝንጅብልን በሻይና በምግባችን ውስጥ እንደ ቅመም በመጠቀም ጤናማና ደስተኛ የሆኑ ጊዚያቶችን ማሳለፍ እንችላለን!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|